ቲዎሪን በተግባር፡ የኢንስቲትዩቱ ሰልጣኞች በቢሾፍቱ የመስክ ምልከታ አካሄዱ ቱ.ማ.ኢ

June 05, 2026
ቲዎሪን በተግባር፡ የኢንስቲትዩቱ ሰልጣኞች በቢሾፍቱ የመስክ ምልከታ አካሄዱ ቱ.ማ.ኢ

ግንቦት 26/2018 ዓ.ም
የፌደራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ሰልጣኞች በክፍል ውስጥ የተማሩትን የንድፈ-ሀሳብ ትምህርት ይበልጥ ለማጠናከር በቢሾፍቱ ከተማና አካባቢዋ በሚገኙ ውብ ሀይቆችና የቱሪስት መዳረሻዎች ላይ የተግባር ልምምድና የመስክ ምልከታ አካሄዱ።
ሰልጣኞቹ በጉብኝታቸው የቢሾፍቱን ታዋቂ ሀይቆች ስነ-ምህዳር እና የቱሪዝም እምቅ አቅም በተጨባጭ ተመልክተዋል፣ የዋና እና የጀልባ ጉዞ (Boating) ልምምድ አድርገዋል፡፡
የባቦጋያ እና ሆራ አርሰዲ ሀይቆች ታሪካዊ አመጣጥ ለአካባቢው ማህበረሰብ ስላላቸው ባህላዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ሰፊ ገለጻ በአስጎቢኚዎች ተደርጎላቸዋል።
በጉብኝታቸው በሆራ ሆራ አርሰዲ እና በቢሾፍቱ ሀይቆች ላይ የሚገኙ የተለያዩ ብርቅዬና ስደተኛ አእዋፋትን የተመለከቱ ሲሆን፣ ስለ አእዋፋቱ ዝርያዎች፣ ባህሪና ስለ ስነ-ምህዳር ጥበቃ ግንዛቤ አግኝተዋል።
በአጠቃላይ ለቱሪዝም ሰልጣኞች በሶስት ክፍል የተዘጋጀው የመስክ ምልከታና የተግባር ስልጠና አስመልክቶ የጉዞው አስተባባሪ እና የቱሪዝም ፋኩልቲ ዲን አቶ ሲሳይ አብርሃም እንደገለጹት ሰልጣኞቹ የወደፊት የቱሪዝም ባለሙያነታቸውንና የአስጎብኚነት ክህሎታቸውን ሊያሳድጉ የሚችሉ ተግባራዊ ልምዶችን የቀሰሙበት ነው ብለዋል፡፡
ይህን መሰል የተግባር ስልጠና የትምህርትን ጥራት ለማሻሻል እና በኢንዱስትሪው ውስጥ በቀጥታ መሰማራት የሚችሉ ብቁና ተወዳዳሪ ባለሙያዎችን ለማፍራት ትልቅ ሚና ይጫወታልም ብለዋል፡፡
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/@ftti_official See less